{"product_id":"ባጭር-የተቀጨ-ረጅም-ጉዞ-bachir-yetekeche-rejim-guzo-መኢሶን-በኢትዮጵያ-ሕዝቦች-ትግል-ውስጥ-meeison-beethiopia-hizboch-tigil-wist-amharic-edition","title":"ባጭር የተቀጨ ረጅም ጉዞ (Bachir Yetekeche Rejim Guzo): መኢሶን በኢትዮጵያ ሕዝቦች ትግል ውስጥ (Me'Eison BeEthiopia Hizboch Tigil Wist) (Amharic Edition)","description":"'ባጭር የተቀጨ ረጅም ጉዞ፡ መኢሶን በኢትዮጵያ ሕዝቦች ትግል ውስጥ' ለንባብ ከበቃ 20 ዓመታት አልፏል። የሚተርከው የዛሬ 45 ዓመት በኢትዮጵያ ስለተካሄደው የ1966 አብዮትና በሐምሌ 1960 ስለተመሰረተው የመኢሶን ሚና ነው። ይህ የፀሐይን የሕትመት ጥራት ደረጃ በተከተለ መልኩ የተሟላ የአርትኦት ሥራን፣ አዳዲስ ታሪካዊ ፎቶግራፎችን፣ እንዲሁም የደራሲውን አዲስ መግቢያና መጠቁም ያካተተ ነው።\nመፅሐፉ መኢሶን ከተመሠረተበት ጊዜ አንስቶ እስከ ነሐሴ 1969 ድረስ ያለውን የመኢሶንን ታሪክና ሚና ይመለከታል። ከ1960 እስከ 1966 በአገር ውስጥና በውጭ በህቡዕ ሲታገል ቆየ። በየካቲት 1966 እንቅስቃሴ ውስጥ ተሳተፈ። በየካቲት 1967 የታወጀው የመሬት ላራሹ አዋጅ በሥራ እንዲተረጎም ታገለ። ከሚያዝያ 1968 እስከ ነሐሴ 1969 በነበሩት 15 ወራት ውስጥ ከደርጉ ጋር ጊዜያዊ ትብብርን መሥርቶ ሠራ። በነሐሴ 14፣ 1969 ከደርጉ ተለየ።\nመፅሐፉ ስምንት ክፍሎች ያሉት ሲሆን በየክፍሉ ሥር በምዕራፎች፣ በአርዕስትና በንዑስ-አርዕስት እየተዘረዘረ የቀረበ ነው። የመጀመሪያው ክፍል ከተማሪ እንቅስቃሴ ወደ ፖለቲካ ድርጅት መቋቋም የተደረገውን ጉዞና የመጀመሪያዎቹን የትግል ዘመናት ይዳስሳል። ሁለተኛው ክፍል የሚያተኩረው በቅድመ-አብዮት ዘመን በነበሩት የመኢሶን\/ኢህአፓ ልዩነቶችና የፖለቲካ ትግሎች ላይ ሲሆን ሦስተኛው ክፍል ደግሞ በየካቲት አብዮት መፈንዳት፣ ሂደትና ክንዋኔ ላይ ይመለሳል። የደረሱትን ሁነቶችና ያስከተሏቸውን ውጤቶች በመዋዕለ-ዜና መልክ ለመከተል ይሞክራል። አራተኛው ክፍል በተለይ የሚመለከተው ከንጉሠ-ነገሥቱ መውርድ እስከ የካቲት የመሬት ይዞታ አዋጅ ድረስ የነበሩትን ጉዳዮች ነው። ዋናውም ጥረት ያንን ብዥ ያለ ዘመን ገለጥ ለማድረግ ነው። ክፍል አምስት ከመሬት ይዞታ አዋጅ እስከ መስከረም 1968 የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ድረስ የነበረውን \"የአንድ እርምጃ ወደፊት፣ ሁለት እርምጃዎች ወደኋላ\" ታሪክ ሲዘግብ፤ በተለይ የሚያተኩረው እየተደራረቡ ይደርሱ በነበሩት የኃይሎች አሰላለፍ ለውጦችና ትንቅንቆች ላይ ነው። ከዚህም ጋር በተያዘ ሂሳዊ\/ገንቢ-ድጋፍ ስለተባለው የመኢሶን መስመር ነው።\nክፍል ስድስት ወደ ብሔራዊ ዲሞክራቲክ አብዮት ፕሮግራም የተደረገውን ጉዞ ያትታል። በሕዝብ ድርጅት ጉዳይ ጊዜያዊ ጽ\/ቤት መቋቋም ታሪክ ላይ ይመለሳል። ክፍል ሰባት ከጽ\/ቤቱ መቋቋም በኋላ መኢሶን ያካሄዳቸውን ትግሎች የሚዘረዝር ነው። በአብዮቱ መግፋትና በተከታታይ በደረሱት የቅልበሳ ሙከራዎች ላይ ተመልሶ የሚተርክ ነው። ክፍል ስምንት የኢትዮጵያ አብዮት መጨንገፍ የጀመረበትን የመጀመሪያ ወቅት ይመለከታል። መኢሶን የትግል ስልት ያደረገበትን የፖለቲካ ምክንያቶች ያቀርባል። በ\"ነጭ\/ቀይ ሽብር\" ጉዳይ ላይ ይመለሳል።\u003cbr\u003eASIN: 1599071126\u003cbr\u003eVSKU: BVV.1599071126.A\u003cbr\u003eCondition: Acceptable\u003cbr\u003eAuthor\/Artist:Assegid, Andargachew\u003cbr\u003eBinding: Hardcover\u003cbr\u003e\u003cb\u003eNote:\u003c\/b\u003e Any images shown are stock photographs and product may differ from what is shown.  \u003cbr\u003e\u003cb\u003eCondition Notes\u003c\/b\u003e: The item is very worn but is perfectly usable. Signs of wear can include aesthetic issues such as scratches, dents, worn and creased covers, folded page corners and minor liquid stains. All pages and the cover are intact, but the dust cover may be missing. Pages may include moderate to heavy amount of notes and highlighting, but the text is not obscured or unreadable. Page edges may have foxing  age related spots and browning . May NOT include discs, access code or other supplemental materials.  \u003cbr\u003e","brand":"Blue Vase Books","offers":[{"title":"Default Title","offer_id":43524146888765,"sku":"BVV.1599071126.A","price":41.86,"currency_code":"USD","in_stock":true}],"thumbnail_url":"\/\/cdn.shopify.com\/s\/files\/1\/0589\/4225\/9261\/files\/1599071126-0.jpg?v=1787865721","url":"https:\/\/www.bluevasebooks.com\/products\/%e1%89%a3%e1%8c%ad%e1%88%ad-%e1%8b%a8%e1%89%b0%e1%89%80%e1%8c%a8-%e1%88%a8%e1%8c%85%e1%88%9d-%e1%8c%89%e1%8b%9e-bachir-yetekeche-rejim-guzo-%e1%88%98%e1%8a%a2%e1%88%b6%e1%8a%95-%e1%89%a0%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab-%e1%88%95%e1%8b%9d%e1%89%a6%e1%89%bd-%e1%89%b5%e1%8c%8d%e1%88%8d-%e1%8b%8d%e1%88%b5%e1%8c%a5-meeison-beethiopia-hizboch-tigil-wist-amharic-edition","provider":"Blue Vase Books","version":"1.0","type":"link"}